Fana: At a Speed of Life!

በህንድና ባንግላዲሽ ከባድ አውሎ ንፋስ ባስከተለው አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012(ኤፍ ቢሲ)አምፋን ተብሎ የሚጠራው ከባድ አውሎ ንፋስ በህንድና ባንግላዲሽ ባስከተለው አደጋ ቢያንስ የ15 ሰዎች ህይወት ማለፈ ተነገረ ፡፡

ዝናብን በቀላቀለው ከባድ አውሎ ነፋስ ህይወታቸው ካለፈው ሰዎች በተጨማሪ በርካቶች ቀያቸውን ለቀው መውጣታቸውም ነው የተገለጸው፡፡

የአምፋን አውሎ ንፋስን ተከትሎ የመሬት ናዳ ተከስቷልም ነው የተባለው፡፡

ከዚያም ባለፈ በዚህ አደጋ 14 ሚሊዮን የሚሆኑ የኮልካታ ነዋሪዎች ኤሌክትሪክና የግንኙነት መስመሮችም መቋረጣቸው ነው የተነገረው፡፡

አለም በኮሮና ቫይረስ ወረርሽን ስጋት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት መከሰቱ ለሃገራቱ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ መሆኑም ተመላክቷል፡፡

የምዕራብ ቤንጋል ዋና ሚኒስትር ማማታ ባነርጄ÷ አደጋው ከኮሮና ቫይረስ የከፋ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በኮልኮታ 3ሺህ 103 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውም ይነገራል ፡፡

ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ እና ሲ.ኤን ኤን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.