Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በአንድ ቀን ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህንድ በአንድ ቀን ከ5 ሺህ በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተሰማ።

በሃገሪቱ 5 ሺህ 242 ሰዎች በአንድ ቀን ብቻ በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 96 ሺህ ደርሷል ተብሏል።

ይህ ቁጥርም ህንድን በቫይረሱ የተያዙ በርካታ ሰዎች የሚገኙባት የእስያ ቀዳሚዋ ሃገር አድርጓታል።

በሌላ በኩል ስፔን ከሁለት ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከመቶ ያነሰ የሟች ቁጥር አስመዝግባለች።

እንግሊዝም እንዲሁ በአንድ ቀን 170 ሞት ያስመዘገበች ሲሆን ይህም የእንቅስቃሴ እገዳ ከተላለፈ በኋላ የመጀመሪያው አነስተኛ ቁጥር መሆኑ ተነግሯል።

በጣሊያን በአንድ ቀን 145 ሰዎች ለህልፈት የተዳረጉ ሲሆን ይህ ቁጥር ከፈረንጆቹ መጋቢት 9 ወዲህ ዝቅተኛ መሆኑ ታውቋል።

በሃገሪቱ ምግብ ቤቶች እንደገና እየተከፈቱ ነው።

 

 

ምንጭ፦ አልጀዚራ እና ቢቢሲ

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.