Fana: At a Speed of Life!

በህንድ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ 18 ሰዎች ለህልፈት ተዳረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 2 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ በደረሰ የአውሮፕላን አደጋ በጥቂቱ 18 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡

ንብረትነቱ የህንድ የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን በደቡባዊቷ ኬራላ ግዛት ካሊከት አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ነው የተከሰከሰው፡፡

አውሮፕላኑ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለችግር የተዳረጉ ህንዳውያንን ከዱባይ ወደ ሃገራቸው ይዞ ከተመለሰ በኋላ በሚያርፍበት ወቅት መጋጨቱም ነው የተሰማው፡፡

በወቅቱ አውሮፕላኑ በውስጡ 190 ሰዎችን አሳፍሮ እንደነበርም ተነግሯል፡፡

የአውሮፕላኑ ሁለት አብራሪዎች ከሟቾቹ ውስጥ እንደሚገኙበት የሃገሪቱ ባላስልጣናት ገልጸዋል፡፡

ከአደጋው የተረፉት ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን 156 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡

አደጋው መንስኤ እየተጣራ ይገኛል ተብሏል፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.