Fana: At a Speed of Life!

በህንድ ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ነፍሰጡር እናቶች ከ100 በላይ ህጻናት ከቫይረሱ ነጻ ሆነው ተወልደዋል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ)በህንድ ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው ነፍሰጡር እናቶች ከ100 በላይ ህጻናት ነጻ ሆነው መወለዳቸው ተሰምቷል።

በምዕራብ ህንድ ሙምባይ የሚገኝ ሆስፒታል በሎክማኒያ ቲልካ ሆስፒታል ባሳለፍነው ሚያዝያ ወር በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ ነፍሰጡር እናቶች 115 ከቫይረሱ ነጻ የሆኑ ህጻናትን ሲያዋልድ ሶስቱ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን፥ ቀሪዎቹ በተደጋጋሚ በተደረገላቸው ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው መረጋገጡ የህክምና ባለሙያወች ተናግረዋል።

በቫይረሱ ከተያዙ እናቶች ውስጥ ሁለቱ በሆስፒታሉ ሲሞቱ አንዷ ልጇን ከመውለዷ በፊት ህይወቷ አልፏል።

በሙምባይ እስካሁን ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን፥ ከ730 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል።

ቫይረሱ ከተገኘባቸው እናቶች አብዛኞቹ ምንም አይነት የቫይረሱን ምልክት አላሳዩም፤ የተቀሩት ትኩሳትና ትንፋሽ ማጠር እንደታየባቸው ተነግሯል።

ከግማሽ የሚበልጡት ህጻናቱ በቀዶ ህክምና ሲወለዱ ሌሎቹ በምጥ ነው የወለዱት።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.