Fana: At a Speed of Life!

በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩ የመረጃ እና የመገናኛ መሳሪያዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ በህገወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ ሊገቡ የነበሩ የመረጃ እና የመገናኛ መሳሪያዎች መያዙን አስታወቀ።

የተያዙት የቴሌኮም ማጭበርበር ለማከናወን የሚያስችሉ 6 መሳሪያዎች (Sim box) መያዙንም ነው የገለፀው።

በዚህም ከ68 ሚሊየን ብር በላይ ማዳን መቻሉን በኤጀንሲው የሴኩሪቲ ክሊራንስ አገልግሎት ማዕከል ኃላፊ አቶ መስፍን ሙሉነህ ገልጸዋል።

ባለፉት 6 ወራት ከቴሌኮም ማጭበርበሪያ መሳሪያዎች በተጨማሪ ለስለላ አገልግሎት የሚውሉ 60 ካሜራዎችን ሀገር ውስጥ ከመግባታቸው በፊት መያዛቸውን አቶ መስፍን አስታውቀዋል።

በቀጣይም የመረጃ እና የመገናኛ መሳሪያዎች ላይ የሚያደረገውን ቁጥጥር ከአጋር አካላት ጋር በመሆን እንደሚሰራ ጨምረው መግለፃቸውን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.