Fana: At a Speed of Life!

ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ግለሰቦች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በልደታ ክፍለ ከተማ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ግለሰቦች ህይወት ማለፉን የአዲስ  አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ሚትሮሎጂ ፊት ለፊት ለልማት በተዘጋጀ ቦታ ላይ በተከሰተው የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ አንድ ግለሰብ በፅኑ ተጎድተው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን  በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ የሆኑት ረዳት ኢንስፔክተር ዳንኤል ታፈሰ ገልፀዋል፡፡

የምርመራ መዝገቡን ዋቢ አድርገው እንዳብራሩት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት አካባቢ አንድ በግምት ዕድሜው ከ50 እስከ 55 የሚገመት ግለሰብ ከሁለት በተመሳይ የዕድሜ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሁለት ሴቶች ጋር እየተገፈታተረ ወደ ቦታው ከገባ በኋላ ፍንዳታ መሰማቱንና ጉዳት መድረሱን ገልፀው÷ የግለሰቦቹ ማንነት እና የፍንዳታው ምክንያት ለማወቅ በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑን መርማሪው ገልፀዋል፡፡

በሠዓቱ የአዲስ አበባ እና የፌደራል ፖሊስ የቴክኒክና የፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች ቦታው ላይ ፈጥነው በመድረስ ተጨማሪ ፍንዳታ እንዳይከሰት አካባቢውን ነፃ የማድረግ ስራ መሰራቱን አስረድተዋል

በተጨማሪም በአንደኛው ሟች ኪስ ውስጥ ተጨማሪ ያልፈነዳ ቦንብ መገኘቱን  ማስታወቃቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.