Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል በመጭው ክረምት 3 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል በመጭው ክረምት 3 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ግብርና ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሚስራ አብደላ እንደገለፁት በክልሉ በመጭው ክረምት 3 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

በተለያዩ የችግኝ ጣቢያዎች ችግኞቹን የማፍላት ስራ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የሚተከሉት ችግኞች የመጽደቅ መጠናቸው እንዲጨምርም ለየአካባቢው ተስማሚ የሆኑና ሀረር የምትታወቅበት የተለያዩ አይነት የፍራፍሬ ችግኞችን ለማፍላት እንዲሁም ችግኝ የማዳቃል ስራ በስፋት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ችግኞቹ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራን ከማጠናከር ባሻገር የክልሉን የደን ሽፋን ያሳድጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በመጥቀስም፥ ህብረተሰቡም ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በእንክብካቤ ስራው ላይ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የተፈጥሮ ሃብት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሻውል በቀለ በበኩላቸው በቀጣዩ ክረምት ለሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ላይ ይተከላሉ ተብለው በተለያዩ የችግኝ ጣቢያዎች የዛፍ፣ የፍራፍሬና የቡና ችግኞች እየተዘጋጁ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተተከሉ ችግኞችም የፅድቀት መጠናቸው 87 በመቶ ላይ ይገኛልም ነው ያሉት።

ችግኞቹ የሚተከሉባቸውን አስር ተፋሰሶችን በመለየትም በቀጣዮቹ ቀናት የበጋ የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ የዘመቻ ስራ እንደሚጀመርም አስረድተዋል፡፡

በተሾመ ኃይሉ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.