Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በጎሎኦዳ ወረዳ 900 ሄክታር መሬት በመስኖ የስንዴ ዘር ተሸፈነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወረዳው በተያዘው የበጋ ግብርና 3 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ መስኖ ለማልማት ታቅዶ 900 ሄክታሩ በዘር ተሸፍኗል ተብሏል።

ከዚህ በተረፈ በ230 ሄክታር መሬት ላይ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጠናቆ ለዘር ዝግጁ መሆኑም ነው የተጠቆመው።

ከዚህ በፊት ስንዴን በፍሬው እንጂ እንዴት እንደሚመረት እንደማያውቁ የተናገሩት የወረዳው አርሶአደሮች ፥ ከግብርና ባለሙያዎች በተሰጣቸው ሙያዊ እገዛ ካለፈው ዓመት ጀምሮ ስንዴን በመስኖ ማምረት መጀመራቸውን ተናግረዋል።

የጎሎኦዳ ወረዳ የግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሀሰን መሀመድ በበኩላቸው፥ የአርሶአደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ምርጥ ዘርና ማደበሪያ በማቅረብ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ወረዳው ከ9 ሺህ በላይ መሬት ስንዴን በመስኖ ለማልማት የሚያስችል ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ግማሹ ብቻ ጥቅም ላይ መዋሉ ነው የተገለጸው።

የወረዳ ምክትል አስተዳዳር አቶ አህመድ ሼክ መሀመድ በበኩላቸው፥ አርሶ አደሮችንና የልማት ሠራተኞች በማቀናጀት ንቅናቄን በመፍጠር የልማት ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል።

በምንያህል መለሠ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.