Fana: At a Speed of Life!

በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 179 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1 ሺህ 179 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመለሱት 1 ሺህ 179 ዜጎች መካከል አንድ ሕጻን እንደሚገኝበትም ነው የተገለጸው፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ ተደርጎላቸው ወደ ማቆያ ማዕከላት መሄዳቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን የመመለስ ሥራም÷ 42 ሺህ 90 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.