Fana: At a Speed of Life!

በቀጣይ 10 ዓመታት ከወጪ ንግድ በየዓመቱ የሚገኘውን ገቢ 9 ቢሊየን ዶላር ለማድረስ ታቅዷል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 15፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ከወጪ ንግድ በየዓመቱ የሚገኘውን ገቢ በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ 9 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማድረስ መታቀዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በ10 ዓመቱ መሪ የልማት እቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
 
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በዚህ ወቅት በቀጣይ 10 ዓመታት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 5 ሚሊየን የስራ ዕድል ለመፍጠር መታቀዱንም ገልፀዋል።
 
በውይይት መድረኩ ላይ የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ እና የ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ የትኩረት መስኮች እንዲሁም በ2012 በጀት ዓመት በጥንካሬና በድክመት የታዩት ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.