Fana: At a Speed of Life!

በታይላንድ የ27 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ወታደር በፀጥታ ኃይሎች ተገደለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 1፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በታይላንድ በንጹሃን ዜጎች ላይ በከፈተው ተኩስ የ27 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ወታደር በፀጥታ ኃይሎች መገደሉ ተነገረ።

ቅዳሜ በተፈጸመው ግድያ የንጹሃን ህይወት ሲጠፋ ሌሎች በርካታ ሰወችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ነው  የታይላንድ ፖሊስ አስታውቋል።

በሰሜን ምስራቅ ታይላንድ ውስጥ 27 ሰዎችን ተኩሶ የገደለው እና 51 ሰወችን ያቆሰለው ወታደር  በታይ የገበያ አዳራሽ ውስጥ የጸጥታ ሀይሎች በወሰዱት መገደሉ ተሰምቷል።

ግለሰቡ በከተማው በመዘዋወር ጥቃት ሲያደርስ፤ በጥቃቱ ወቅት የራሱን ፎቶ የማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ መለጠፉ ታውቋል።

ጥቃት አድራሹ ወታደር  ጃክራፓንት ቶማ የገበያ አዳራሹን ቢቆጣጠርም ፖሊስ  ሁሉም ገበያተኞች በሰላም ከአዳራሹ እንዲወጡ ማድረጉን አስታውቋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.