Fana: At a Speed of Life!

በአስር ከተሞች የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ማሻሻያ ተግባራዊ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እያጋጠመ ያለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ችግርን ለመቅረፍ የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ማሻሻያ ፕሮጀክት በተመረጡ 10 ከተሞች ተግባራዊ ሊያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በማሰራጫ መስመሮች እርጅና ምክንያት በከተሞች አካባቢ እያጋጠመ ያለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዠቅ ችግር ለመቅረፍ ነው ማሻሻያ የሚደረገው፡፡

ፕሮጀክቱ በአዲስ አበባ፣ በነቀምት፣ በአምቦ፣ በሱሉልታ፣ በቢሾፍቱ፣ በአሰላ፣ በደብረ ብርሃን፣ በዲላ፣ በሆሳዕና፣ በአሶሳ እና በጅግጅጋ ከተሞች ነው ተግባራዊ የሚደረገው፡፡

ፕሮጀክቱ የከተሞችን የኃይል ፍላጎት መሸከም የሚችል የማሰራጫ መስመር በመዘርጋት እየተፈጠረ የሚገኘውን መቆራረጥና የኃይል መዋዠቅ ችግር ለመቅረፍ ይረዳል ተብሏል፡፡

ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ የሚውለው 100 ሚለየን ዶላር ከዓለም ባንክ የሚገኝ ሲሆን፥ በሶስት ዓመታት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞለታል፡፡

በአራት ሎት ተከፍሎ የሚከናወነው ይህ ፕሮጀክት፤ በአጠቃላይ 1 ሺህ 610 ነጥብ 60 ኪሎ ሜትር የሚሆን የመካከለኛ ቮልቴጅ መስመር ማስፋፊያና ማሻሻያ ስራን የሚያካትት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.