Fana: At a Speed of Life!

በአሶሳ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 107 የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሶሳ ከተማ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በተገኙ 107 የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታውቋል፡፡
 
የቢሮው ሃላፊ አቶ ለሜሳ ዋወያ እንደገለጹት÷ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በወቅታዊ የጸጥታ ጉዳይ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደው መስመር መስተጓጎሉን ተከትሎ በርካታ የንግድ ድርጅቶች በፍጆታ እቃዎች እንዲሁም አትክልትና ፍራፍሬዎች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ አድርገው ነበር፡፡
 
በከተማው የተስተዋለውን አላስፈላጊ የሆነ የዋጋ ጭማሪ የሚቆጣጠር ግብረ-ኃይል ወደሥራ መግባቱን የገለጹት ኃላፊው፥ አሳማኝ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ አድርገው በተገኙ 107 የንግድ ድርጅቶች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል፡፡
 
ግብረ-ኃይሉ ባካሄደው የክትትልና ቁጥጥር ሥራ 54 የንግድ ድርጅቶችን የማሸግ እና 53 የንግድ ድርጅቶችን ደግሞ ከከባድ እስከ ቀላል ማስጠንቀቂያ መሰጠቱን አስረድተዋል፡፡
 
በተያያዘም የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን ምርቶች በማከማቸት ለተጠቃሚው ማኅበረሰብ ሊያቀርቡ የነበሩ የንግድ ድርጅቶች እርምጃ እንደተወሰደባቸው መናገራቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሙኒኬሸን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ከመንገዱ መስተጓጎል ጋር ተያይዞ እጥረት ተከስቶባቸው የነበሩ የነዳጅና የቤንዚን እጥረት ለመፍታት ከሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ጋር እየተሠራ ስለመሆኑም አንስተዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.