Fana: At a Speed of Life!

በኻሾግጂ ግድያ ጥፋተኛ ተብለው የተያዙ ስምንት ግለሰቦች ላይ ከ8 እስከ 20 ዓመት ተፈረደባቸው

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሳዑዲ አረቢያ በጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ ግድያ ጥፋተኛ ብላ የያዘቻቸው ስምንት ግለሰቦች ላይ ከ8 እስከ 20 ዓመት የእስር ቅጣት አስተላለፈች፡፡
 
ከዚህ ቀደም በአምስቱ ግለሰቦች ላይ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸው እንደነበረ የሚታወስ ነው፡፡
 
አሁን ላይ ከስምንቱ ግለሰቦች መካከል አምስቱ 20 ዓመት የተፈረደባቸው ሲሆን ሦስቱ ከ7 እስከ 10 ዓመት እንደተፈረደባቸው የሳዑዲ አረቢያ የዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡
 
ይህ የሆነው የኻሾግጂ ልጅ በግንቦት ወር ጥፋተኛ ተብለው ለተያዙት ግለሰቦች ይቅርታ ማድረጉን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡
 
ጋዜጠኛ ጀማል ኻሾግጂ በ2011 በመስከረም ወር መጨረሻ በቱርክ በሚገኘው የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡
 
ምንጭ፦አልጀዚራ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.