Fana: At a Speed of Life!

በጀርመን የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ምዕራባውያን የአሸባሪው ህወሃትን ኢሰብዓዊ ድርጊቶች በማጤን አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን መንግስትን ጨምሮ ምዕራባውያን የአሸባሪውን ቡድን ኢሰብዓዊ ድርጊቶች እንዲገነዘቡና አቋማቸውን እንዲያስተካክሉ በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጠየቁ።

በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ለተወከሉ የጀርመን አባላት፣ ለፓርላማው ፕሬዚዳንት እና ለአምስቱ ዋነኛ የጀርመን ፓርቲዎች መሪዎች በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያላቸውን አቋም የሚገልፅ ደብዳቤ ልከዋል።

በመግለጫቸውም÷ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋርና በአማራ ክልሎች ያካሄዳቸውን ወረራዎች፣ በህፃናት፣ ሴቶች እና አቅመ ደካሞች ላይ የፈጸማቸውን ኢሰብዓዊ ድርጊቶች፣ ጥቃቶች፣ ግድያዎች፣ መፈናቀሎችና ዝርፊያዎችን አውግዘዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በጋራ ያወጡት ሪፖርት እውነታውን የገለጠና የአሸባሪውን የህወሓት ቡድን የሃሰት ፕሮፖጋንዳዎች ያጋለጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የአንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት ጫና እና የሚዲያዎቻቸው ዘመቻ እንዲሁም አሜሪካ በኢትዮጵያ የአጎዋ ተጠቃሚነት ላይ ያሳለፈችው ውሳኔ ፍትሃዊነት የጎደላቸው ተግባራት መሆናቸውን ነው ያመለከቱት፡፡

ኢትዮጵያውያኑና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ በዚሁ የአቋም መግለጫቸው፥ የምዕራባውያን እና የአሜሪካንን ጫና ተከትሎ ዳያስፖራው በአሜሪካ፣ በብራሰልስ፣ በዩናትድ ኪንግደም እና በጀርመን የተቀጣጠለውን የ”በቃ” ዓለም አቀፋዊ የተቃውሞ ንቅናቄ አድንቀዋል፡፡

በደብዳቤያቸው፥ የአውሮፓ ሕብረት እና በጀርመን መንግስት አሸባሪው የህወሓት ቡድን የሚፈጽማቸውን ወረራዎች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እውቅና ተሰጥተው በግልጽ ማውገዝ እንዳለባቸው ነው ያመለከቱት።

በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሚሰራጩት መረጃዎች ሚዛናዊ የሆነ ሪፖርት ላይ እንዲመሰረቱ ብሎም አሳሳችና ሀሰተኛ ዘገባዎችን እንዲቆሙም አሳስበዋል።

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማዕቀብ አውግዘው ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤነውም ጠይቀዋል።

በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያን መንግስት ኃላፊነት ማክበር እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ለሚያካሂዱት ልማት እና የመልሶ ግንባታ ሥራዎች ብሎም ለአፍሪካ ቀንድ ሠላም አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.