Fana: At a Speed of Life!

በ2012 በጀት አመት በብድር እና በእርዳታ ከ106 ቢሊየን ብር በላይ ተገኝቷል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 22 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በ2012 በጀት አመት በብድር እና በእርዳታ 106 ነጥብ 875 ቢሊየን ብር ማግኘቷን አስታወቀ፡፡

ከዚህ ውስጥ 37 ነጥብ 38 ቢሊየን ብሩ ከተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት እና ለጋሸ ሀገራት በብድር የተገኘ ነው፡፡

69 ነጥብ 495 ቢሊየን ብሩ ደግሞ አዲስ ብድር እና እርዳታ መሆኑም ነው የተነገረው፡፡

ይህም በበጀት አመቱ ለማግኘት ከታቀደው 81 ነጥብ 3 በመቶ አፈጻጸም ማሳየቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በተያያዘ ዜና በበጀት አመቱ ለፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ ከውጭ የገንዘብ ምንጮች 142 ነጥብ 297 ቢሊየን ብር መገኘቱንም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ፍሰቱ ካለፈው ተመሳሳይ አመት ጋር ሲነጻጸር የ27 ነጥብ 296 ቢሊየን ብር ብልጫ አለው።

በፕሮጀክቶች አፈጻጸም የታየው መሻሻል እንዲሁም አሱን ተከትሎ የለጋሽ ሀገራት እምነት መጠናከሩ ለአፈጻጸሙ ማደግ አስተዋጽኦ ነበረው ተብሏል፡፡

በዳዊት በሪሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.