Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ሁለት ቀናት 12 የጠላት ጦር የአርሚና የኮር ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ

ሰበር ዜና
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 15 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ቀናት በተካሄደ ልዩ ዘመቻ 12 የጠላት ጦር የአርሚና የኮር ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ።
 
የእቅድ፣ የአመራር እና የቴክኖሎጅ እውቀትን በመጠቀም መንግስት ባለፉት ቀናት በባቲ ግንባር በወሰደው የማጥቃት እርምጃ ስድስት የህወሓት የአርሚና የኮር ከፍተኛ አመራሮች መደምሰሳቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገልጸዋል።
 
ሚኒስትሩ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ እርምጃ የተወሰደባቸው የጠላት ጦር ከፍተኛ አመራሮች በሃገር ክህደት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።
 
በዚህም የወገን ጦር ሰብአዊና ቁሳዊ ኪሳራን በሚቀንስ መልኩ በቀየሰው ስትራቴጂ እርምጃ መውሰዱንም ገልጸዋል።
 
በከሚሴ ግንባርም በተመሳሳይ በዛሬው እለት በተወሰደ እርምጃ ስድስት የአርሚና የኮር ከፍተኛ አመራሮች መደምሰሳቸውን ነው የገለጹት።
 
የተደመሰሱትም የጠላትን ጦር ሲመሩ የነበሩ ኮሎኔል እና ጄኔራሎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
 
በባቲ ግንባር ዛሬ በተወሰደ እርምጃም ለመልሶ ማጥቃት የተዘጋጀውን ሃይል በማያዳግም እርምጃ መደምሰስ መቻሉን እና የተረፈውም እግሬ አውጭኝ ብሎ እንዲፈረጥጥ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።
 
በሌሎች ግንባሮችም የወገን ጦር በሰነዘረው ከፍተኛ የማጥቃት እርምጃ ጠላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተመታ ይገኛል ብለዋል ሚኒስትሩ በመግለጫቸው፡፡
 
ህብረተሰቡም የወገንን ጦር ጥቃት መቋቋም አቅቶት በቡድን እና በተናጠል እየሸሸ ያለው የጠላት ሃይል ጉዳት እንዳያደርስ አካባቢውን በንቃት እንዲከታተልም ጥሪ አቅርበዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!የእቅድ፣
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.