Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 28 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸው ሲያልፍ 707 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 26፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 28 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።
 
የጤና ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገፃቸው ባለፉት 24 ሰዓታት 7 ሺህ 607 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ተደርጎላቸው 707 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው አስታውቀዋል።
 
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 18 ሺህ 706 ደርሷል።
 
በአሁኑ ወቅትም 153 የፅኑ ህሙማን በህክምና ላይ እንደሚገኙ የጤና ሚኒስትሯ ገልፀዋል።
 
በትናንትናው ዕለትም 406 ሰዎች ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ 601 ሆኗል።
 
በኮሮናቫይረስ የተነሣ የሞቱ ሰዎች ቁጥርም 310 ደርሷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.