Fana: At a Speed of Life!

ኒያላ ኢንሹራንስ ለህዳሴ ግድብ የ26 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዢ ፈፀመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የ26 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ቦንድ ግዢ ፈፀመ።

በስነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦች ኩባንያው ለፈፀመው የቦንድ ግዢ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር የዛሬውን ቦንድ ግዢ ጨምሮ ላለፉት 10 ዓመታት በአጠቃላይ ከ90 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዢ መፈፀሙ ተገልጿል።

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ እስካሁን በህዝብ ተሳትፎ 17 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተነግሯል።

የቦንድ ግዢው ስነ- ሥነ ስርዓት ላይ የግድቡ ግንባታ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት የቦርድ አባት፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ታዊቂ ግለሰቦችን ጨምሮ የኒያላ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ያሬድ ሞላ ተገኝተዋል።

በመለሰ ምትኩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.