Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለግብጽ የ197 ሚሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ አጸደቀች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ አዲሱ አስተዳደር ለግብጽ በ197 ሚሊየን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማጽደቁን አስታወቀ፡፡

አስተዳደሩ 168 የአጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ለግብጽ ለመሸጥ ነው ውሳኔ ያሳለፈው፡፡

የሽያጩ መጽደቅ ግብጽ ከሚነሳባት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ ግብጽ የጦር መሳሪያ ግዢውን የፈጸመችው በባህር ዳርቻዎቿ አካባቢዎችና በቀይ ባሕር ዙሪያ የመከላከያ ኃይሏን ለማጠናከር መሆኑን ገልጿል፡፡

የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አሜሪካ ከግብጽ ጋር የሚኖራት ስትራቴጂካዊ ግንኙነት እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡

የቀድሞው የአሜሪካ አስተዳደር ከግብጹ መሪ ጋር የተሻለ ግንኙነት እንደነበረው ይታወሳል፡፡

ሆኖም አሁን በስልጣን ላይ የሚገኙት ጆ ባይደን ከሰብዓዊ መብት ጋር በተያያዘ ጠንካራ አቋም እንዳላቸው ይነገራል፡፡

በዚህም ከአብዱል ፈታ ኤልሲሲ መንግስት ጋር ቅራኔ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ ተብሏል፡፡

ይህንን በማስመልከትም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተሉት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አሜሪካ ባለፈው ሳምንት ሳዑዲ በየመን ለምታካሂደው ጦርነት የምታደርገውን ድጋፍ ማቋረጧን አስታውቃለች፡፡

በተጨማሪም የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶችን የጦር ጀት ግዢ ጉዳይ ዳግም እንደምታጤነውም ገልጻለች፡፡

ምንጭ፦ አልጀዚራ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.