Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው የህወሃት ጁንታ ዳግም እንዲመለስና ንፁሃንን እንዲጨፈጭፍ አንፈቅድም-የሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ማህበረሰብ

 

አዲስ አበባ፣ህዳር 19፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ሚኒሶታ እና አከባቢው የሚኖሩ የሶማሌ ክልል ተወላጆች እና ዲያስፖራ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ሀገር የማዳን ትግል ድጋፋቸውን ገልፀዋል።

ዛሬ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች የተውጣጡ የዲያስፖራ አባላት በኢትዮጵያ እና በህዝቦቿ ላይ ምዕራባዊያን እና አሸባሪ ህወሃት ለመመለስ የሚያደርጉት ዘመቻና እንቅስቃሴ ፍፁም ተቀባይነት የለውም ብለዋል።

ባለፉት ሦስት አስርተ አመታት አሸባሪው ህወሃት በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ በተለይ በሶማሌ ክልል ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል እና ግፍ የሚረሳ አይደለም ብለው፣ አሁን ላይ ከአሸባሪው ቡድን ጋር ዳግም ጋብቻን ፈጥረው የሶማሌ ክልል ህዝብን እንወክላለን የሚሉት የመላው ሶማሌ ህዝብ ጠላት ናቸው ብለዋል።

በሚኒሶታ በተካሄደው የድጋፍ ኮንፈረንስ ላይ ዲያስፖራው ከለውጡ በኋላ በነፃነት በመንቀሳቀስ በሶማሌ ክልል በሰፈነው አስተማማኝ ሰላም በከተሞች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፈሰስ እንደቻሉ ገልፀው፣ ባለፉት ሦስት የለውጥ አመታት የተገኘውን ሰላምና ልማት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እንደሚታገሉ መግለፃቸውን ከሶማሌ ክልል ብዙሃን መገናኛ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሚመራው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ለሚመራው የሶማሌ ክልል መንግሥት እና ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሶማሌ ክልል ዲያስፖራ ማህበረሰብ ሙሉ ድጋፍ እንዳለውም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀገርን ከጥፋት ለማዳን ግንባር ድረስ በመሄድ ሠራዊቱን ለመምራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ቆራጥና ጠንካራ መሪ መሆናቸው ያሳያልም ነው ያሉት የዲያስፖራ አባላቱ።

በውጭ ሀገር ተቀምጠው በኢትዮጵያ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በማህበራዊ ሚዲያዎች ዲያስፖራውን ለማሳሳት የሚደረጉ እንቅስቃሴን በመታገል ከህልውና ዘመቻው አካል ከመሆን ባሻገር፣ ሀገሪቷ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እንዳይገጥማትና ወገን እንዳይቸገር ገንዘብ በህጋዊ መንገድ እንዲላክ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.