Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን  በተለያዩ አገራት ከተሾሙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር  ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን  በቅርቡ በተለያዩ አገራት ከተሾሙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ጋር  ውይይት አካሄዱ።

አቶ ደመቀ  ውይይቱን ያካሄዱት በቅርቡ በአውስትራሊያ፣ ጋና፣ ጣሊያን፣ ቱርክ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ደቡብ ሱዳንና ሴኔጋል ከተሾሙ የኢትዮጵያ  አምባሳደሮች ጋር  ነው።

ተሿሚ አምባሳደሮቹ በተሾሙባቸው አገራት በፖለቲካ ዲፕሎማሲ፣ ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ዘርፎች የሚያከናውኗቸውን ተግባራት የያዘ የ100 ቀናት እቅድ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

አቶ ደመቀ መኮንን የአምባሳደሮችን እቅድ መሰረት በማድረግ በሰጡት የስራ መመሪያ የተመደቡባቸው አገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል

እንዲሁም የዜጎች  መብት፣ ጥቅምና ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራትን በትኩረት ማከናወን አለባችሁም ነው ያሉት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በበኩላቸው÷ አምባሳደሮቹ ስራዎቻቸውን ሲያከናውኑ ከኢትዮጵያ  አስፈጻሚ ተቋማት ጋር ጥብቅ ትስስር በመፍጠር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንዖት ሰጥተው ገልፀዋል።

ሚኒስትሩ አያይዘውም በአሁኑ ወቅት የሀሰት መረጃዎች በስፋት በማሰራጨት የአገራችንን መልካም ገጽታ ለማጉድፍ የተወሰኑ አካላት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሰው÷   ለዲጂታል ዲፕሎማሲ ስራዎች ትኩረት በመስጠት ተጨባጩን የኢጥዮጵያን  ሁኔታ  ማስገንዘብ እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.