Fana: At a Speed of Life!

አቶ ጃንጥራር አባይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በመገኘት የአቅመ ደካሞችን ቤት እድሳት አስጀምረዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት የከተማ አስተዳደሩን ጥሪ በመቀበል በኮቪድ19 ወረርሽኝ ሳቢያ ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን በመደገፍ ላይ ያሉ ባለሃብቶችን እና በጎ ፍቃደኛ ግለሰቦችን አመስግነዋል፡:

መጭውን አዲስ ዓመትም ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን በማሰብ እና ያለውን በማካፈል መቀበል ይገባል ብለዋል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፍቃዱ ካሳሁን በበኩላቸው በክፍለ ከተማው በክረምት በጎ ፍቃድ መርሃ ግብር እስካሁን 66 የአቅመ ደካማ ቤቶችን በማደስ ለባለቤቶች ማስረከባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ዛሬ የተጀመሩትን ጨምሮ 121 ቤቶችን እስከ ነሃሴ ወር መጨረሻ ድረስ አጠናቆ ለማስረክብ እየተሰራ መሆኑን አቶ ፍቃዱ ተናግረዋል፡፡

በዛሬው ዕለት በተካሄደ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብርም በሶስት ዙሮች ባለሃብቶችን በማስተባበር ሶስት ሚሊየን ብር የሚገመት የሁለት ወር አስቤዛ ለ500 እማወራ እና አባዎራዎች ድጋፍ ተደርጓል ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.