Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካውያን የኢትዮጵያን ትግል እንዲቀላቀሉ ምሁራን የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ምሁራን ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ትግል እንዲቀላቀሉ ኢትዮጵያውያን ምሁራን የመሪነት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዶክተር ምህረት ደበበ ገለጹ።

የአካዳሚው አመራሮችና ሠራተኞች ዛሬ ለአገር መከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ፣ በተለያዩ አካባቢዎች እገዛ ለሚሹ ዜጎችም ድጋፍ አድርገዋል።

ዶክተር ምህረት በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ÷ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የሕልውና ማስከበር ትግል ከዓለም አቀፍ ፍላጎቶች ጋር ጭምር ነው።

ጦርነቱ የጠብመንጃ ብቻ ሳይሆን የሃሳብም ጭምር በመሆኑ ምሁራን ይህንን በመመከት ረገድ የማይተካ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል።

ምሁራን ኢትዮጵያ የያዘችውን እውነት ለዓለም በማሳወቅና የአፍሪካን ምሁራንም በመቀስቀስ የሃሳብ ጦርነቱ አካል እንዲሆኑ በማድረግ አገራዊ ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

ግዙፍ ዓለምአቀፍ ሚዲያዎችና የጥናትና ትምህርት ተቋማት ከኢትዮጵያ በተቃራኒ ቆመዋል ያሉት ዶክተር ምሕረት ÷ ይህንንም የተሳሳተ አካሄድ በመመከት እውነታውን ለዓለም ማሳወቅ እንደሚገባም አውስተዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነፃነት ፋና ወጊ በመሆኗ “ኢትዮጵያን ማንበርከክ ማለት አፍሪካን ማንበርከክ ነው” በሚል እሳቤ ዘመቻ መከፈቱን ጠቅሰዋል።

ጦርነቱ ሕልውናችንን ሊገዳደር የሚችል ዓለም አቀፋዊ ባሕሪ ያለውና የኢትዮጵያን ዕጣ ፈንታ የሚወስን በመሆኑ ምሁራን በአደባባይና በጋራ ልንናገር ይገባል ነው ያሉት።

የአካዳሚው የቲንክ ታንክ እና ማማከር አገልግሎት ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን አረጋ ÷ ምዕራባውያን አገራትና ሚዲያዎቻቸው የሚያደርጉትን ጫና ለመመከት በምሁራን ተሳትፎ በምን መልኩ መስራት እንደሚገባ ምክክር እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል አካዳሚው ለመከላከያ ሠራዊትና ለተፈናቃይ ዜጎች ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ኢዜአ ዘግቧል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.