Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ በጤናው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ ጉብኝት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የሩዋንዳ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ዳንኤል ኔሚጄ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒዬም ኮሌጅን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም የሆስፒታሉን የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥና እና የሕክምና ትምህርት ፕሮግራሞች ን ተመልክተዋል፡፡
የሩዋንዳው የጤና ሚኒስትር የልምድ ልውውጥና ጉብኝትም በሁለቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች መካከል ያለውን ትብብርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ሚኒስትሮቹ በቀጣይ በጤናው ዘርፍ የሚያደርጉትን ትብብር ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ከሆስፒታሉ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.