Fana: At a Speed of Life!

ከ129 ሚሊየን ብር በላይ የሚገቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር ከሐምሌ 27 እስከ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ከ129 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች፣ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የታክስ ማጭበርበሮች ተደርሶባቸው ለመንግሥት ገቢ መደረጉን አስታወቀ።

ከዚህ ውስጥ 449 ሺህ 700 የአሜሪካ ዶላር በሁመራ መስመር እንዲሁም 46 ሚሊየን ብር የሚገመት 23 ሺህ ግራም ወርቅ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ከሀገር ሊወጣ ሲል መያዙን አስታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ አልባሳት፣ ሞተር ሳይክሎች፣ የጦር መሣሪያዎች፣ ጌጣጌጦች፣ አደንዛዥ ዕፆች፣ በጎብኚዎች ስም እና በሕገ ወጥ መንገድ የገቡ ተሽከርካሪዎች እና ሌሎች ዕቃዎች የጉሙሩክ ሕግን በመተላለፍ ሲዘዋወሩ ተይዘዋልም ነው ያለው፡፡
እንዲሁም ሊጭበረበር የነበረ ታክስ በተደረገ ክትትል እንደተያዘ ማስታወቁን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከዚህ ባለፈም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሕገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ክላሽንኮቭ፣ የክላሽንኮቭ ካዝና፣ የክላሽ ጥይቶች፣ ሽጉጦች፣ የሽጉጥ እና የብሬን ጥይቶች መያዙንም ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.