Fana: At a Speed of Life!

ኪም በደቡብ ኮርያ ባለስልጣን ግድያ ይቅርታ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰሜን ኮርያው ፕሬዚዳንት ኪም ጁንግ ኡን በደቡብ ኮርያ ባለስልጣን ግድያ ይቅርታ መጠየቃቸው ተሰማ፡፡

ኪም ባልተለመደ መልኩ ይቅርታ መጠየቃቸውን የገለጹት የደቡብ ኮርያ ባለስልጣናት ናቸው ተብሏል፡፡

የሁለቱ ኮርያዎች ድንበር በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ጥብቅ ቁጥጥር የሚደረግበት ሲሆን ሰሜኖቹ ወደ ሀገራቸው ለመግባት የሚሞክሩት ላይ እንደሚተኩሱ ነው የተሰማው፡፡

ግድያ የተፈጸመባቸው የ47 ዓመቱ ባለስልጣን በሰሜኖቹ የውሃ ክፍል ላይ አስከሬናቸው ሲንሳፈፍ ማግኘታቸውን ነው ወታደሮች የገለጹት፡፡

ባለስልጣኑ በተተኮሰባቸው ጥይት ከተመቱ በኋላ በእሳት መቃጠላቸው ደቡቦቹ የገለጹ ቢሆንም ሰሜኖቹ ግን ግለሰቡ የያዟቸው ቁሳቁሶች ያነሱት መሆኑን በደብዳቤያቸው አስፍረዋል፡፡

ከአስር ዓመት በኋላ አንድ ደቡብ ኮሪያው በሰሜኖቹ ግድያ ሲፈጸምበት ይህ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡

 

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.