Fana: At a Speed of Life!

ኬንያ ከኮቪድ 19 የህክምና ቁሳቁስ ግዢ ጋር በተያያዘ በሙስና የጠረጠረቻቸው ባለስልጣናትን ልትከስ ነው

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፍተኛ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ የኬንያ ባለስልጣናት ከኮቪድ 19 የህክምና ቁሳቁስ ግዢ ጋር በተያያዘ በሙስና ተጠርጥረው ክስ ሊከፈትባቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ባለስልጣናቱ ከኮቪድ 19 የህክምና ቁሳቁስ ግዢ ጋር በተያያዘ በሚሊየን የሚቆጠር ዶላር መዝብረዋል ነው የተባለው፡፡

ከባለስልጣናቱ መተጨማሪ በአገሪቱ የሚገኙ ያለአግባብ የተጠቀሙ ነጋዴዎችም እንደሚጠየቁ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ባለስልጣናቱ ከጨረታ ህግ ውጪ በፖለቲካዊ እሳቤ ከነጋዴዎች ጋር መመሳጠራቸው ተነግሯል፡፡

የአገሪቱ ጸረ ሙስና ኮሚሽንም ህግ ያልተከተሉ ወጪዎችንም በምርመራ ማረጋገጡን አሳውቋል፡፡

የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ የተከሰተውን ነገር በፍጥነት እንደሚጣራ ቃል ገብተዋል፡፡

የኬንያ ፀረ ሙሽና ኮሚሽን ለአገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሪፖርቱን አቅርቧል፡፡

ሪፖርቱን ተከትሎም ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር አውሎ ክስ እንደሚመሰርት ይጠበቃል፡፡

በኬንያ በአሁኑ ወቅት 37 ሺህ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ 24 ሺህ የሚሆኑት አገግመዋል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.