Fana: At a Speed of Life!

የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ተሽከርካሪዎች መቐለ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ የህክምና ቁሳቁስ የጫኑ ተሽከርካሪዎች ዛሬ መቐለ መግባታቸውን የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በኢትዮጵያ አስታውቋል፡፡
 
በ5ኛ ዙር መቐለ የገቡት የኮሚቴው ተሽከርካሪዎች÷የህክምና ቁሳቁስ፣ የምግብ ድጋፎችን፣ የውሃ ማጣሪያ ግብዓቶችን እና አስፈላጊ የቤት ቁሳቁስ የያዙ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ተመሳሳይ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በትናንትናው ዕለት በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙ ሁለት መጠለያ ጣቢያዎች ለሚኖሩ 9 ሺህ ዜጎች የምግብ ድጋፍ ማድረጉን ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.