Fana: At a Speed of Life!

የሊቢያ የሰላም ድርድር የሽግግር መንግስት ሳይሰየም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሊቢያ ድርድር ጊዜያዊ አዲስ የሽግግር መንግስት እና የፕሬዚዳንት ምክር ቤት ሳይሰየም ተጠናቀቀ፡፡

በሊቢያ የተባበሩት መንግስታት መልዕክተኛ ስቴፋኒ ዊሊያምስ በሃገሪቱ አዲስ የሽግግር መንግስት እንዳልተሰየመ ተናግረዋል፡፡

በድርድሩ ተፋላሚ ወገኖቹ በ18 ወራት ውስጥ በሃገሪቱ በሚካሄደው ምርጫ ፍኖተ ካርታ ላይ መስማማታቸው ይታወሳል፡፡

በውይይቱ የምርጫ ሂደቱን የሚታዘብ የሽግግር ጊዜ አስተዳደር ማቋቋምን ያለመ መሆኑ ተጠቅሶ የነበረ ቢሆንም የሽግግር መንግስቱ ሳይሰየም መጠናቀቁ ነው የተነገረው፡፡

ሆኖም ተደራዳሪዎቹ በጊዜያዊነት ሊቢያን የሚመራ የሽግግር መንግስት ለመምረጥ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ለመገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን አስታውቀዋል፡፡

ውይይቱ የተካሄደው በጎረቤት ሃገር ቱኒዚያ ሲሆን የሰላም ድርድሩ ባለፈው ወር በጄኔቫ በተፎካካሪ ወገኖች መካከል የተፈረመውን የተኩስ አቁም ስምምነት ተከትሎ ሰኞ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡- አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.