Fana: At a Speed of Life!

የሬማ ከተማ ነዋሪዎች ለሰራዊቱ ከ200 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳወረሞ ወረዳ ሬማ ከተማ ነዋሪዎች በወሎ ግንባር ለተሰለፈው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ200 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የአይነት ድጋፍ አድርገዋል።
 
የሚዳወረሞ ህዝባዊ ድጋፍ አስተባባሪ ወ/ሮ ባዩሽ ስመኝ እንደተናገሩት፣ አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለመበታተን የሽብር ተግባራትን ቢፈፅምም ሀገራችን በጀግኖች ልጆቿ ሳትደፈር እንደታፈረች እና እንደተከበረች ለዘላለም ትኖራለች ብለዋል።
 
የሽብር ቡድኑ ከኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ እስኪደመሰስ እና ሃገራችን ወደ ቀደመው ሠላሟ እስክትመለስ ድረስ ለመከላከያ ሠራዊታችን የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.