Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር ከጂ አይ ዜድ ኢትዮጵያ ጋር ድንበር ዘለል የትብብር ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር ጂ አይ ዜድ ኢትዮጵያ ጋር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በብሉ ናይል ድንበር ዘለል የትብብር ስምምነት ተፈራረመ።
የሰላም ሚኒስቴር የፌዴራሊዝምና አርብቶ አደር ጉዳዮች ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ስዩም መስፍን÷ ስምምነቱ በአካባቢው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ድርቅን ለመቋቋም የሚያስችልና የገቢ ምንጫቸውን በማስፋት አቅማቸውን ለማሳደግ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሴቶችና ወጣቶች የሰላም ዘብ እንዲሆኑ ለማድረግ ግጭቶችን እንዴት መፍታት እንደሚችሉ ስልጠናዎችን መስጠት እና በሁለቱ ድንበር ላይ የጋራ ልማት መፍጠር የስምምነቱ አካል እንደሆነም ገልፀዋል።
የጂ አይ ዜድ ሀላፊ ማይኢክ ቫን ኡም በበኩላቸው÷ ፕሮግራሙ ተፈፃሚ የሚሆነው በአውሮፓ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ሃላፊው አያይዘውም ፕሮግራሙ በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2021 ድረስ ቀጣይነት እንዳለው መናገራቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.