Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ሚኒስቴር “ፌዴራሊዝምና ሰላም ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር እየተወያየ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር “ፌዴራሊዝምና ሰላም ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡

በውይይቱ መክፈቻ ላይ በሰላም ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ የፌዴራል ስርዓቱ በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መልኩ የህብረተሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ በህብረተሰቡ ያሉ የተዛቡ አመለካከቶችን በማስተካከል የአገርን ሰላምና አንድነት ለማስጠበቅ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡

አቶ ካይዳኪ፥ ባለፉት ጊዜያት የፌዴራል ስርዓቱ ሚዛኑን ጠብቆ እየተገነባ እንዲሄድ የሚያስፈልጉ ከእውቀትና ግንዛቤ ማነስ ጀምሮ አዳዲስና ወቅታዊ የህዝብ ጥያቄዎችንና ፍላጎቶችን በተገቢው መንገድ ለመመለስ የሚያስችል ብቃት ያልነበራቸው እንደነበሩ ነው የገለጹት፡፡

ስለሆነም በፌዴራል ስርዓቱ ላይ የተዛቡ ብዥታዎችን ለመቅረፍና የህብረተሰቡን ጥያቄዎች በአግባቡ ለመመለስ እንደነዚህ ያሉ ውይይቶችን በማካሄድ የመንግስት አካላትን ብቃት ለማሳደግና የህብረተሰቡንም ግንዛቤ ለማስፋት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የህዝብ ተወካዮች፣ የፌዴሬሽንና የክልል ምክር ቤቶች አባላት፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና የሰላም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.