Fana: At a Speed of Life!

የሱዳን ልዑላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን አስመራ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሱዳን ልዑላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ገብተዋል።

ለአንድ ቀን የስራ ጉብኝት አስመራ የገቡት ሊቀመንበሩ በኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል እንደተደረገላቸው የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ሁሉቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ እየታየ ያለውን መሻሻል በተመለከተ እና በሌሎች ሁለቱን ሀገራት በሚጠቅሙ የጋራ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሏል።

የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ከስልጣን ከነተሱ በኋላ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱ ይነገራል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.