Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ሚሊሻ እና ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊዎች ወደ ግንባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልል ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አለማየሁ ጢሞቲዎስ እና የሚሊሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ኪኤ የጠቅላይ ሚኒሰትሩን ጥሪ በመቀበል ወደ ግንባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን ገለጹ፡፡
 
ሃገርን ማዳን ቅድሚ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ያሉት አቶ አለማየሁ÷ ከዚህ በፊት ለመዝመት ቅድመ ዝግጅት አድረገው እንደንደነበር አንስተዋል፡፡
 
በአሁኑ ሰዓትም ሁለት የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች በግንባር እንደሚገኙ ነው የተናገሩት፡፡
 
መሪነትም ሆነ ሌሎች ነገሮች መኖር የሚችሉት ሀገር ሲኖር በመሆኑ በቀጣይም ዘመቻው ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ነው ያሉት ሃላፊው ፡፡
 
ልጆችን ለማሳደግም ሆነ በክብር ለመቀበር ሀገር ያስፈልጋል ያሉት ሃላፊው÷ሽፍታ ደምስሰን የሀገር ሉዓላዊነቷን አስከብረን የማትደፈርና ታሪኳ በድጋሜ በወርቅ መዝገብ ላይ እስኪፃፍ ድረስ እኔም ለመሰለፍ ዝግጁ ነኝ ሌሎቹም አመራሮች ዝግጁ ናቸው ብለዋል፡፡
 
የክልሉ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ በረከት ኪኤ በበኩላቸው÷ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሀገርን ለማዳን ያሳዩትን ቁርጠኝነት በማድነቅ በግላቸው በዘመቻው የመሳተፋ ጉዳይ ቀድሞም ፍላጎት እንደነበራቸውና አሁንም ቢሆን ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ እዘምታለው ብለዋል፡፡
 
ለኢትዮጵያ አንድነትና ፍቅር እንዲሁም ለህዝባቸው እያበረከቱ ላለው አበርክቶም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አድናቆት አለኝ ያሉ ሲሆን ሌሎች አመራሮችም በዚህ ልክ ዝግጁ መሆን እንደሚገባው አንስተዋል፡፡
 
በብርሃኑ በጋሻው
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.