Fana: At a Speed of Life!

የቪዥን ብራይት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት አባላት ወደ ግንባር እንደሚዘምቱ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቪዥን ብራይት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት አባላት ወደ ጦር ግንባር እንደሚዘምቱ ገለጹ።
 
የቪዥን ብራይት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት አባላት አሸባሪው ህወሓትን ለመፋለም ወደ ጦር ግንባር እንደሚዘምቱ የድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ ወጣት ሞቲ ሞሮዳ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
 
በጎ አድራጎት ድርጅቱ ባለፉት 3 ዓመታት በሀገር ሰላምና ልማት ላይ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን የገለጸው ወጣቱ አሁን ደግሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጦሩን ለመምራት ወደ ግንባር መዝመታቸውን ተከትሎ የድርጅቱ አባላት ለመዝመት ተነሳስተዋል ብሏል።
 
ወጣቶቹ የአሸባሪው ህወሓትን ሀገርን የማፍረስ እኩይ ሴራ ለማክሸፍ ህይወቱን እየሰዋ ካለው መከላከያ ሰራዊት ጎን ለመሰለፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጧል።
 
የቪዥን ብራይት ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ከተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተውጣጡ ከ50 ሺህ በላይ ወጣት አባላት እንዳሉትም ተገልጿል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
 
 
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.