Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተለያየ የሙያ መስክ ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች እያስመረቁ ነው፡፡
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሰቲ እና ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው፡፡
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ታፈረ መላኩ እንደገለጹት÷ ዩኒቨርሲቲው ዛሬና ነገ እያካሄደ ባለው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ 2 ሺህ 108 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ ሆኖ መመደቡን ተከትሎ በግብርና፣ በሀገርበቀል እውቀትና በጤና ዘርፎች በትኩረት እየሠራ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል፡፡
በተመሳሳይ ደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 353 እጩ መምህራን ዛሬ አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 176 ያህሉ ሴቶች ናቸው።

 

በተመሳሳይ የሰዎች ለሰዎች የቴክኒክና አግሮ ኮሌጅ በተለያዩ ሙያዎች ያሰለጠናቸውን 116 ተማሪዎች በዲግሪ መርሃ ግብር አስመርቋል፡፡
ኮሌጁ ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የአግሮ ቴክኒክና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ተማሪዎችን ተቀብሎ እያሰለጠነ ሲሆን÷ በዘንድሮው ዓመትም በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ፣ ማኑፋክቸሪንግና ኤሌክትሪካልና ኤሌክትሮኒክስ የትምህርት ዘርፎች ለአራት ዓመት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።
ኮሌጁ በኢትዮጵያ የተመዘገበ የውጭ የሲቪል የማህበረሰብ ድርጀት ሲሆን ÷ በሐረር ከተማ በዶክተር ካርል ሄንዝ በም ስም የተመሰረተ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.