Fana: At a Speed of Life!

የተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለአንድ ቻይና ፖሊሲ ያላቸውን ድጋፍ ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እ.ኤ.አ. በ1971 የወጣውን የተባበሩት መንግስታት ጠቅላላ ጉባኤ የአንድ ቻይና ፖሊሲን በመደገፍ ያሳለፈውን ውሳኔ ዛሬም እንደሚደግፉ ገለፁ።
የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲን የታይዋን ጉብኝት አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ “አቋማችን በጣም ግልፅ ነው” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
ይህንንም ሲያብራሩ “በጠቅላላ ጉባኤ በተላለፈው ውሳኔ መሰረት፥ የአንድ ቻይና ፖሊሲን እናከብራለን፤ ይህም በስራችን ሁሉ የሚገዛን አካሄድ ነው ” ሲሉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
እ.ኤ.አ. ጥቅምት 25 ቀን 1971 የተላለፈው የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔ፥ የቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ መንግስት የቻይና ብቸኛ ህጋዊ ተወካዮች አድርጎ እውቅና ሰጥቷል፡፡
ይህ የውሳኔ ሃሳብ ቻይና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ካላቸው ሀገራት መካከል ቻይና አንዷ እንድትሆንም እውቅና የሰጠ ነው።
ምንጭ፡- ሲጂቲኤን
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.