Fana: At a Speed of Life!

የተጠያቂነትን ሥርዓት በማጎልበት የዕቅድ አፈፃፀም ብቃትን ማሳደግ ይገባል – ዶ/ር ፍጹም አሰፋ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ የተጠያቂነትን ሥርዓት በማጎልበት የዕቅድ አፈፃፀም ብቃታችንን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሳደግ ይገባናል ሲሉ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ ይህን ያሉት÷ በመንግስት ተቋማት የ100 ቀን ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ግምገማ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡
የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ባካሄደው ግምገማ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የ100 ቀን ዕቅድ ትግበራ ላይ ግምገማ ተካሄዷል።
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ ላይ በተካሄደው ግምገማ ገምጋሚ ቡድኑ ላነሳቸው ጥያቄዎች ዶክተር በለጠ ሞላ እና ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በዚሁ ወቅት ዶክተር ፍጹም በዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ የተጠያቂነትን ሥርዓት በማጎልበት የዕቅድ አፈፃፀም ብቃታችንን ቀጣይነት ባለው መልኩ ማሳደግ ይገባናል ብለዋል፡፡
ክትትልና ግምገማ መንግስት ትክክለኛውን ተግባር በአግባቡ እየከወነ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ብቸኛው ስልት እንደሆነም ጠቁመዋል።
እያንዳንዱ የመንግስት ተቋም የየራሱ መገለጫ ቢኖረውም እቅዶች ወደ ተግባር ተለውጠው ውጤት ማስመዝገባቸውን መከታተልና ግምገማ ማድረግ ይጠበቅበታል ማለታቸውን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.