Fana: At a Speed of Life!

 የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ህግን በተላለፉ ከ130 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ህግን በተላለፉ ከ130 ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
 
ቢሮው የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ህግን በአግባቡ በመቆጣጠር ነዋሪዎችን ከእንግልትና ተጨማሪ ክፍያ ለመከላከል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
 
በዚህ መሰረትም ህግ ለማስከበር በሰራው ስራ በመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ህግን በተላለፉ 130 ሺህ 472 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ነው የተገለጸው፡፡
 
በነዚሁ ጥፋተኞች ላይ በተወሰደ እርምጃም 19 ሚሊየን 630 ሺህ ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉንም ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ቅጣቱ የተጣለው ትርፍ በመጫን፣ ከታሪፍ በላይ በማስከፈል፣ ከተመደቡበት ርቀት በታች አቆራርጠው በመጫን፣ ታፔላ ባለመስቀል እንዲሁም ተያያዥ ጥፋቶችን በመፈጸማቸው ነው፡፡
 
በቀጣይም የክትትልና ቁጥጥር ስራውን በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር በመዘርጋት አሰራሩን ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
 
በተለይ በበዓላትና በምሽት ወቅት መመሪያን በሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተጠቁሟል፡፡
 
ከትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዞ የተቀመጠውን መመሪያ በመተግበር የትራንስፖርት እጥረት እንዳይከሰት አሽከርካሪዎች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.