Fana: At a Speed of Life!

የቻይና-የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሰላምና ልማት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሀገራት ተወካዮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና-የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት የሰላምና ልማት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሀገራት ተወካዮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡

ነገ ለሚጀመረው የመጀመሪያው የሰላምና ልማት ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛን ዡ ቢንግን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች አዲስ አበባ መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የጉባዔው ተሳታፊዎች ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካከለኛው ምስራቅ፣ የኤዥያና ፓሲፊክ ጉዳዮች ዳይሬክተር-ጄኔራል አምባሳደር ዶክተር ገበየሁ ጋንጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቻይና የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት በፀጥታ፣ ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ያሉባቸውን ተግዳሮቶች እንዲፈቱ ለማገዝ እንደምትሰራ ስትገልፅ ቆይታለች።

ሀገሪቱ በምስራቅ አፍሪካ ሠላም እና ብልጽግና እንዲረጋገጥ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗንም ነው የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በቅርቡ በአካባቢው ሀገራት ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት የተናገሩት፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.