Fana: At a Speed of Life!

የአቃቂ ጨፌ ሁለት የተማከሉ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎች ተመረቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአቃቂ ጨፌ ሁለት የተማከሉ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎችና የላቦራቶሪ እና አስተዳደር ህንጻ ተመርቀዋል።

ጨፌ 2 እና 3 የፍሳሽ ማጣሪያዎች እያንዳንዳቸው 12 ሺህ 500 በድምሩ 25 ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ በቀን የማጣራት አቅም አላቸው።

ፕሮጀክቶቹ ከ423 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ሰዎች አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሲሆን፥ በቀን የነበረውን 148 ሺህ ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ወደ 173 ሺህ ከፍ ያደርጉታልም ነው የተባለው።

ሶስቱ ፕሮጀክቶች የተሰሩት በመንግስት በጀት ሲሆን፥ ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል።

ፕሮጀክቱን መርቀው የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፥ አዲስ አበባን ውብና ጽዱ ለማድረግ እንዲህ አይነት ስራዎች በየጊዜው አቅደን መስራት ይገባል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ የከተማዋን ፍሳሽ ቆሻሻን ከማስወገድ በተጨማሪ የማህበረሰቡን ጤና በመጠበቅ ረገድም ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።

የከተማዋ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ በበኩላቸው፥ አሁን የተመረቁት ፕሮጀክቶች የከተማዋን ፍሳሽ ቆሻሻ የማስወገድ አቅም እንደሚጨምሩ ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ አሁን ላይ 164 ሺህ ሜትር ኪዩብ የማጣራት አቅም ያላቸውን የደቡብ አቃቂ እና የምስራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያዎችን ለመገንባት በሂደት ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.