Fana: At a Speed of Life!

የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ያስከተለው የጎርፍ አደጋ በርካታ ጉዳቶችን እያደረሰ ነው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) ዘንድሮ ለየት ባለ ሁኔታ የአዋሽ ወንዝ ሞልቶ ያስከተለው የጎርፍ አደጋ በርካታ ጉዳቶችን እያደረሰ ነው።

ወንዙ አቅጣጫ በቀየረበት አፋር ክልል ደግሞ ዜጎች እንዲፈናቀሉና ንብረታቸው እንዲወንድም ከማድረጉ ባለፈ የደረሱ ምርቶችን ከጥቅም ውጪ አድርጓል።

የተከሰተው የውሀ ፍሰት ባስከተለው የጎርፍ አደጋ በአንድ ወረዳ ብቻ ከ14 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የደረሰ ምርት አውድሟል።

በዚህም የሸንኮራ አገዳና ጥጥ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ምርቶች መሆናቸው ተገልጿል።

አብዛኛው ከጥቅም ውጪ የሆነው የደረሰና ከመስከረም አራት ጀምሮ ሊሰበሰብ የነበረ ምርት መሆኑም ተመላክቷል።

ከዚያም ባለፈ በደረሰው ውድመት በእርሻ ልማት ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችና አርሶ አደሮች ለከፍተኛ ችግር እየተዳረጉ መሆናቸው ተገልጿል።

በዚህም የአሚባራ መካከለኛ አዋሽ የእርሻ ልማት ድርጅትን ብቻ ከ 1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሞበታል።

ድርጅቱ በስሩ በተለያየ መንገድ ቀጥሮ የሚያሰራቸው 5 ሺህ የሚደርሱ ሰራተኞች ስራ መፍታታቸው ተነግሯል ።

በ6 ሺህ 17 ሄክታር መሬት ከ1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት የደረሰ ምርት የወደመ ሲሆን÷ በመገልገያ እቃዎች ላይም ከ300 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገልጿል።

የገጠመውን ችግር ለመፍታትም የክልል እና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ መሆኑ ነው የተገለፀው።

በኃይለኢየሱስ ስዩም

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.