Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ትብብር መጠናከር ለአህጉራዊ ትብብር ወሳኝ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ትብብር መጠናከር ለአህጉራዊ ትብብር ወሳኝ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ናይጄሪያ መግባታቸው ይታወቃል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሶ ሮክ በተሰኘው የፕሬዚዳንት ቤተ መንግሥት በፕሬዚዳንት ሞሐመዱ ቡሃሪ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በመቀጠልም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ልዑክ ከናይጄሪያ ልዑካን ቡድን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርጓል።
ከውይይቱ በኋላም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ፥ ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ታላላቅ የአፍሪካ ሀገራት መሆናቸውን ጠቁመው፥ “የእኛ ትብብር መጠናከሩ ለሁለትዮሽ ግንኙነታችን እንዲሁም ለአህጉራዊ ትብብር ወሳኝ ነው” ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፕሬዚዳንት ሞሐመዱ ቡሃሪ ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበልም ምስጋና አቅርበዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.