Fana: At a Speed of Life!

የእስያ ፓሲፊክ ሃገራት ትልቁን የንግድ ህብረት መሰረቱ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዓለምን አንድ ሦስተኛ የምጣኔ ሃብት የያዙት 15 ሃገራትን ያቀፈው የእስያ ፓሲፊክ የንግድ ህብረት መመስረቱን ሃገራቱ ይፋ አደረጉ፡፡

ስምምነቱ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ምጣኔ ሃብታቸው ለተጎዱ ሃገራት መልካም ነገር ይዞ ይመጣል ተብሏል፡፡

የተመሰረተው የምጣኔ ሃብት ትብብር በ20 ዓመታት ውስጥ ወደ የሃገራቱ በሚገቡ ምርቶች ላይ ቀረጥን ሙሉ ለሙሉ እንደሚያነሳ ነው የተገለጸው፡፡

ሃገራቱ 29 በመቶ የሚሆነውን የዓለምን የምጣኔ ሃብት ሲይዙ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው የዓለም ህዝብ እንደሚኖርባቸው መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በዚህ የንግድ ስምምነት ከእስያ ሃገራት መካከል ህንድ ያለመካተቷ የተገለጸ ሲሆን ፈራሚዎቹ በራቸው ለህንድ ክፍት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ የንግድ ስምምነት ከአሜሪካ፣ ሜክሲኮ ካናዳ የንግድ ስምምነትና እና ከአውሮፓ ህብረት የንግድ ስምምነት እንደሚበልጥም ተጠቅሷል፡፡

በዓለም አቀፍ ምጣኔ ሃብት ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት የንግድ ስምምነቱ በየዓመቱ 186 ቢሊየን ዶላር ወደ ዓለም ምጣኔ ሃብት እንደሚያስገባ ጠቅሰዋል፡፡

አባል ሃገራቱ ደግሞ በየዓመቱ የ0 ነጥብ 2 በመቶ ዕድገት እንደሚያስመዘግቡ ነው ያነሱት፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.