Fana: At a Speed of Life!

የከተማ አስተዳደሩ ገቢዎች ቢሮ በግማሽ በጀት ዓመቱ 21 ነጥብ 53 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ በግማሽ በጀት ዓመቱ 21 ነጥብ 53 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

ቢሮው በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት 23 ነጥብ 79 ቢሊየን ለመሰብሰብ አቅዶ የዕቅዱን 94 ነጥብ 46 በመቶ መሰብሰብ መቻሉን ገልጿል።

አፈፃፀሙ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ2 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር ወይም የ13 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ እንዳለውም ነው የገለጸው።

ገቢው ቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆነ ግብር እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የተገኘ ነው ተብሏል።

ቢሮው በ2012 በጀት ዓመት 37 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ ይዞ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.