Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልና የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሠራዊት ከ91 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልና የተለያዩ ተቋማት ለመከላከያ ሠራዊት ከ 91 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ አደረጉ፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለመከላከያ ሰራዊት ከ77 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ፡፡

የክልሉ ህዝብ ለጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት 1 ሺህ 198 ሠንጋዎች፣ 108 የበግና ፍየል፣ 60 ኪሎ ግራም የሚቆዩ ምግቦች ፣ 164 ኪሎ ግራም ቅቤ፣ 410 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም የእህል ምግቦች ጨምሮ በዓይነትና በጥሬ ገንዘብ በአጠቃላይ ከ77 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሃብት ድጋፍ አድርጓል ብለዋል ።

በግንባር ጉዳት ለደረሠባቸው የመከላከያ ሠራዊት አባላትም  ደም መለገሱን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የጅማ ከተማ የትምህርት ማህበረሰብ ለአገር መከላከያ ሰራዊ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

 

በተያያዘ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ፣ የሀይማኖት ተቋማት እና የደሸት ባህላዊ የእፅዋት ምርምር ተቋም ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነት እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁስ ድጋፍ አበርክተዋል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ባለስልጣን ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች “ደማችንን ለመከላከያ ሰራዊታችን” በሚል መሪ ሀሳብ ለመከላከያ ሠራዊት የደም ልገሳ መርሐ ግብር ማከናወናቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል፡፡

በወርቃአፈራው ያለው፣ ተጨማሪ መረጃ የመከላከያ ሰራዊት ገፅና የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.