Fana: At a Speed of Life!

የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አባላት ለህብረ ብሔራዊነት መጠንከር ሊሰሩ ይገባል- የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 1፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት አባላት የህገ መንግሥት የበላይነት እንዲረጋገጥና ህብረ ብሔራዊነትን ለማጠናከር ሊሰሩ እንደሚገባ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ ገለፁ።
ምክር ቤቱ በተሻሻለው የአሠራርና የአባላት ስነምግባር ደንብ ዙሪያ ለ6ኛ ምርጫ ዙር የክልል ምክር ቤት አባላት ስልጠና እየሰጠ ነው።
በሥልጠና መድረኩ ላይ የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ባንቻየሁ ድንገታ ባስተላለፉት መልእክት፥ የክልል ምክር ቤት የተጣለበትን የህዝብ አደራ በአግባቡ ለመወጣት የተሻሻለው የአሠራርና የአባላት ሥነምግባር ደንብ ተግባራዊ በማድረግ ምክር ቤቱ ሀላፊነቱን እንዲወጣ ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል።
የምክር ቤቱ አባላት የመረጣቸው ህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ለማድረግ በየጊዜው የሚነሱ ጥቆማዎችና አቤቱታዎችን መሠረት በማድረግ ከህዝቡ ጋር በመገናኘት ውይይት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ገልፀዋል።
የምክር ቤት አባላት ከሙስናና ብልሹ አሠራር በመታቀብ በፀረ ሙስና ትግል ግንባር ቀደም ሆኖ መገኘት አለባቸውም ነው ያሉት።
ሥልጠናው ለ2 ቀናት በሚኖረው ቆይታ የተሻሻለው የአሠራርና የአባላት ሥነ-ምግባር ሠነድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም ሥልጠናው በክልሉ ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና በሀብት ማሳወቅና ምዝገባ እንዲሁም በፌዴራሊዝም ዙሪያ የተዘጋጁ የውይይት ሠነዶች ቀርበው እንደሚወያዩበት ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.