Fana: At a Speed of Life!

የጭፍራ ጤና ጣቢያ በቀጣይ ሳምንት አገልግሎት መስጠት ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በአሸባሪው ህወሃት የወደመውን የጭፍራ ጤና ጣቢያ መልሶ በማደራጀት በቀጣይ ሳምንት ወደ ስራ እንደሚያስገባ አስታወቀ።
ሆስፒታሉ ከጤና ተቋማት መልሶ ግንባታው ባሻገር ጭፍራ አካባቢ የተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ሁለት ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የጤና ተቋማትን መልሶ የማቋቋሙ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ መሆኑን የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የአገልግሎት ምክትል ፕሮቮስት ዶክተር ሊዲያ ተፈራ ተናግረዋል፡፡
ሆስፒታሉ ከዚህ ቀደም በአሸባሪው ህወሃት ቡድን ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበትን የደሴ ሆስፒታልን መልሶ በማደራጀት አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረጉን አስታውሰዋል፡፡
አሁን ላይ ደግሞ አሸባሪ ቡድኑ ያወደመውን የጭፍራ ጤና ጣቢያ መልሶ የማቋቋም ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው÷ ጤና ጣቢያውን መልሶ በማደራጀት በቀጣይ ሳምንት ስራ ለማስጀመር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኮሌጁ ጤና ጣቢያውን ወደ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማሳደግ ግብዓቶችን እያዘጋጀ መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.