Fana: At a Speed of Life!

ዩኒቨርሲቲዎች ሰላማዊ እንዲንሆኑ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የኦሮሚያና አማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደቱ ሰላማዊ እንዲንሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለፁ።

በኦሮሚያ እና አማራ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ የምክክር መድረክ ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ሲካሄድ ቆይቷል።

የውይይት መድረኩ በሁለቱም ክልሎች ባሉ ዩኒቨርስቲዎችበሚከሰቱ ግጭቶች ዙሪያ በመምከር የመፍትሄ ሃሳብ ለመጠቆም ያለመ ነው።

ከዚህ ባለፈም ውይይቱ በሁለቱ ክልሎች ህዝቦች መካከል ያለውን የእርስ በርስ ግንኙነትና ትስስር ይበልጥ በማጠናከር ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑ ተመላክቷል።

እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተቀራርበው በቅንጅት እንዲሰሩ እና የፖለቲካ ዓላማቸውን እና ተግባራቸውን በተለያዩ አካባቢዎች ለደጋፊዎችቻው እንዲያሳውቁየሚያስችል መሆኑም ታውቋ።

ለሁለት ቀናት ሲካሄደ የቆየው ውይይትም በዛሬው እለት የጋራ መግለጫ በማውጣት በዛሬው እለት ተጠናቋል።

በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያለው ግጭጥ እንዲቆም እና የመማር ማስተማር ሂደት ሰላማዊ እንዲንሆን የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

መንግስትም በተማሪዎች መካከል ግጭት የሚፈጥሩ አካላት ተጠያቂ እንዲያደርግ በመግለጫቸው ጠይቀዋል።

የከፍተኛ ተቋማት ጥበቃ እንዲጠናከርም አሳስበዋል።

በአዳነች አበበ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.